
ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብር የተቸገሩትን በመጠየቅና በመረዳዳት ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) 1ሸህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ቻግኒ ከተማ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር ሃይማኖቱ በሚያዘው መሰረት በመረዳዳትና በመጠያየቅ ሊሆን እንደሚገባም የጓንጓ ወረዳ የሸሪአ ፍርድ ቤት ዳኛና የቻግኒ ከተማ ዑለማ ምክርቤት ሰብሳቢ ሼህ አብዱ እንድሪስ ለእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳች መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ዓመቱ ብዙዎች መጥፎ የተመኙለት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት የተጠናቀቁበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የሀገር አፍራሹን አሸባሪ ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሚደረገው የህልውና ዘመቻም ሕዝበ ሙስሊሙ ያልተቆጠበ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በበዓሉም ለህልውና ዘመቻ በግንባር ላይ ለሚገኙት ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ከ20 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ተሰብስቧል፡፡
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
