በጣና ሃይቅ ላይ ስትጓዝ የተሰወረችው ጀልባ ካፒቴን አስከሬን መገኘቱን የምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

298

በጣና ሃይቅ ላይ ስትጓዝ የተሰወረችው ጀልባ ካፒቴን አስከሬን መገኘቱን የምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በጣና ሃይቅ ላይ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችን ጀልባ መሰወር ተከትሎ ፖሊስ ተሳፋሪዎችን ለማግኘት የተጠናከረ አሰሳ እያደረገ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ፖሊስ ባደረገው አሰሳ ትናንት የሰባት ሰዎች አስከሬን መገኘቱን አስታውቆ ነበር፡፡ ቀሪ ሰዎችን ለማግኘት ፖሊስ አሰሳውን መቀጠሉን መናገሩንም አሚኮ ዘግቦ ነበር፡፡ ፖሊስ ባደረገው አሰሳም የጀልባዋ ካፒቴን አስከሬን መገኘቱን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ ለአሚኮ ገልጸዋል፡፡

ጀልባዋ የተሰወረችው በወረዳው አዲሰጌ ድንጌ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ መነሻዋን በማድረግ ወደ ጎርጎራ ጉዞ ከጀመረች በኋላ ነው።

ተጓዦቹ ሐምሌ 9/2013 ዓ.ም ሌሊት እስከ 15 ኩንታል የሚደርስ ድንች ጭነው ጉዞ መጀመራቸውን ፖሊስ ከቤተሰቦቻቸው ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ መግለፁ የሚታወስ ነው።

ጀልባዋ ከመዳረሻዋ ከመድረሷ አስቀድሞ ሰምጣ አልያም በማዕበል ተወስዳ ሊሆን ይችላል በሚል ፍለጋ መቀጠሉን ፖሊስ ገልፆ ነበር፡፡ እስካሁን በተደረገ ፍለጋም በድምሩ የስምንት ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል፡፡ ቀሪ ሰዎችን ለማግኘት አሰሳ እንደሚቀጥልም ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በአዲስ አበባ በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
Next articleሕዝበ ሙስሊሙ የአረፋ በዓልን ሲያከብር ከተለያዩ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት ማሳለፍ እንደሚገባ የደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼህ ከድር ሁሴን ተናገሩ፡፡