
1 ሽህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በደሴ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
ባሕር ዳር:ሐምሌ 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከማለዳ ጀምሮ በተክቢራና በሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች በዓሉን እያከበሩ ነው፡፡
የከተማዋ ሙስሊሞች በፉርቃን መስጅድ የኢድ ሶላት አድርሰዋል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳትና የተፈናቀሉ ወገኖቹን በመጠየቅ ሊሆን እንደሚገባ ያነጋገርናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ገልጸዋል፡፡

የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት በመከናወኑም ደስታ እንደተሰማቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ለሀገር ሰላም በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ – ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m
