የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢድ አል አድሃ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

359
የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢድ አል አድሃ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሽህ 442ኛው ለኢድ አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት ለሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የሰላምና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በዓሉን ሲከበር እርስ በርስ በመረዳዳት፣ አቅመደካሞችን በመርዳትና ወንድማማችነት በተሞላበት ሁኔታ አቅም ያላቸው የተቸገሩትን በመርዳት መሆን ይገባዋል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት የሀገር ጠንቅ የሆነው አሸባሪው ሕወሓት የሀገርን ሰላም ለማናጋት የጀመረውን ትንኮሳ በጋራ መከላከል አለብን ብለዋል።
ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ ሁለተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ የውኃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከሶማሌ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የዒድ አል-አድሐ ዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት በዓል ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን አስመልዕክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Next articleየኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓልን እንዴት እያከበራቸሁ ነው?