የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ስናከብር ሕዝበ ሙስሊሙ ለተቸገሩ እዝነት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ የጎንደር ታላቁ መስጊድ አስተዳዳሪ አሳሰቡ።

110
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ስናከብር ሕዝበ ሙስሊሙ ለተቸገሩ እዝነት በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ የጎንደር ታላቁ መስጊድ አስተዳዳሪ አሳሰቡ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለ1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጎንደር ታላቁ መስጊድ አስተዳዳሪ ሃጂ ማሩፍ ኑሩሴን ናቸው።
በዓሉ ሲከበር የነብዩን ትዕዛዛት በመከተል ለተቸገሩ ሰዎች ድጋፍ በማድረግ መሆን እንደሚገባው ገልጸዋል።
በሀገሪቱ የተፈጠረውን ችግር ለማለፍ ለዘመቱ የሚሊሻ፣ የልዩ ኀይል እና መከላከያ ሠራዊት አባላት ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የዘመቱ የጸጥታ አካላት በሰላም እንዲመለሱ እና ሀገር ሰላም እንድትሆን ካለፈው ሳምንት ጀምሮም ሕዝበ መስሊሙ በየመስጊዱ ጸሎት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:–ዳንኤል ወርቄ— ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleለህልውና ትግሉ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡
Next article“እኛ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማንሻገረው ችግር የለም” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች