የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እንዲሁም እርስ በእርስ በመተሳሰብ እና በመተጋገዝ የኢድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል ማክበር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

91
የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እንዲሁም እርስ በእርስ በመተሳሰብ እና በመተጋገዝ የኢድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል ማክበር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢድ አል አድሐ አረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አቶ ደመቀ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል
ለመላው ሙስሊም ወገኖች
ለ1442ተኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢድ አል~አድሓ ዓረፋ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አብሮ አደረሰን።
በዕምነቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት እንዲሁም እርስ በርስ በመተሳሰብ እና በመተጋገዝ በዓሉ በደስታ እንድናሳልፍ እመኛለሁ።
በዚሁ አጋጣሚ እንደሀገር ከፊትለፊት ለሚጠብቁን የጋራ የቤት ሥራዎች በአንድነት ስሜት በመተሳሰብ እና በመደጋገፍ ሀገራዊ ኀላፊነታችንን እንድንወጣ አደራ ለማለት እወዳለሁ።
መልካም የዓረፋ በዓል!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleፕሬዘዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ለኢድ አል አድሐ ( አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
Next article“የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ የኢትዮጵያዊያን ልዩ የድል ብስራት ቀን ነው” ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ