
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የውኃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው የውኃ ሙሊት ተከናውኗል፡፡
የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ የውኃ ሙሊትን አስመልክቶ እንዳሉት
ሁለት ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውኃ መጠን ይዘናል፡፡
የውኃ ሙሊቱም በስኬት መጠናቀቁን ነው ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ የገለጹት፡፡
የሠራናቸው ሥራዎች ውጤት ማምጣት ጀምረዋል ያሉት ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ በዚህም የኢትዮጵያን ሕዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡
ኃይል አመንጭተን ሕዝባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ እንሠራለን ነው ያሉት ዶክተር ኢንጅነር ስለሽ፡፡
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ጎረቤት ሀገሮችም የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
