
በስቶክሆልም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ ገቢ ተሰበሰበ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም(አሚኮ) በስትኮልም የኢፌዴሪ ኤምባሲ ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ገቢ አሰባስቧል።
በገቢ አሰባሰቡ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የውጊያ አውሮፕላን አብራሪ የነበሩ እና በስቶክሆልም ከተማ ነዋሪ መቶ አለቃ አበያ በቀለ በልጆቻቸው ስም የሦስት ሺህ የአሜሪካ ዶላር የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል።
መቶ አለቃ አበያ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያጋጠማትን የውስጥ እና የውጭ ስጋቶች ለመሻገር ባላቸው ሙያ ሀገራቸውን እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡
በስዊድን ስቶኮልም የኢፌዴሪ አምባሳደር ድሪባ ኩማ መቶ አለቃ አበያ ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል። ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ድጋፍ እንዲያደርጉና የውጭ ጫና በመመከት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳመላከተው የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በኖርዲክ ሀገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ መነሳሳት ፈጥሯል።
የሁለተኛ ዙር ሙሌት ከተጀመረ ወዲህ አስር ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ የቦንድ ሽያጭ በኤምባሲው መከናወኑም ተመላክቷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
