
የጁንታውን ቡድን ለመደምሰስ የሚደረገውን ዘመቻ ለማገዝ ወደ ግንባር ለሚያቀናው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ኃይል አሸኛኘት ተደረገለት።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም(አሚኮ) የጁንታው ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ሀገር የመበታተን ተግባር ሙሉ በሙሉ በማክሸፍ የሕዝቦችን አንድነት መመለስ የልዩ ኃይሉ ዓላማ መሆኑን የክልሉን ፕሬዝዳንት በመወከል አቶ ቢኒያም መንገሻ ተናግረዋል።
በፖለቲካው መድረክ ሽንፈትን የተከናነበው ጁንታው በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀበራቸው የተንኮል ፈንጅዎች ችግር የፈጠሩ ቢሆንም በሰላም ወዳዱ ሕዝብና በሠራዊቱ ከፍተኛ ጥረት ሐሳቡ እንዳይሳካ ተደርጓል ነው ያሉት።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው ይህ አጥፊ ቡድን ከውጭ የሀገራችን ጠላቶች ጋር በመቀናጀት የፈጸመው እኩይ ተግባር ምንጊዜም የታሪክ ተወቃሽነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ አደራ የተሰጣቸው የልዩ ኃይል አባላት በድል አድራጊነት እንደሚመለሱ ሙሉ እምነት እንዳላቸው መግለጻቸውን ከመተከል ዞን ኮምዩኒኬሽን መምሪያ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
