ምክር ቤቱ በግድቡ ድርድር የተገኘውን የዲፕሎማሲ ድል በሕዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

167
ምክር ቤቱ በግድቡ ድርድር የተገኘውን የዲፕሎማሲ ድል በሕዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ በአፍሪካ ሕብረት እንዲታይ ሲል ያሳየውን ድጋፍ በሕዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ።
ዶክተር አረጋዊ በተለይ እንደገለጹት የህዳሴው ግድብ ድርድር ወደ አፍሪካ መምጣቱን ተከትሎ በሕዝብ ዘንድ የተፈጠረውን መነቃቃት በተደራጀ መልኩ ለግድቡ ግንባታ አቅም እንዲሆን ለማስቻል እየተሠራ ነው።
‹‹ትስስር ለህዳሴ ግድብ›› በሚል መሪ ሀሳብ ሕዝቡን በማደራጀት አስተዋፆው እንዲጨምር ለማድረግ በሀገር ውስጥም በውጭም ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፤ በአንድነት መሥራት ውጤት የሚያመጣ በመሆኑ ለወደፊትም ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
አሁን የተገኘውን የዲፕሎማሲ ድል ለማስቀጠል ጠንክሮ መሥራትና የሕዝቡን ተሳትፎ በየዘርፉ ማሳደግ ያስፈልጋል ያሉት ዋና ደይሬክተሩ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያን ወዳጆች በማደራጀት ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የሀገር መከላከያ ሠራዊት አሁን ላይ በሀገራዊ እይታና አንድነትን በሚያስጠብቅ ቅኝት ተደራጅቷል” ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ
Next articleለዘመቻ ህልውና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታቸውን በተግባር እያሳዩ መሆናቸውን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች ገለጹ።