በኒውዮርክ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአጣዬና ከሚሴ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ 75 ሽህ ዶላር በላይ ድጋፍ አሰባሰቡ።

114
በኒውዮርክ እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአጣዬና ከሚሴ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ 75 ሽህ ዶላር በላይ ድጋፍ አሰባሰቡ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ)
በአማራ ክልል በተለያየ አካባቢዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን ለማቋቋም በሃገር ውስጥና በውጭ ሀገሮች እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማስገንዘብና ለዚሁ እንቅስቃሴ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ የገቢ ማሰባስቢያ መርኃግብር በአሜሪካ ተካሂዷል።
በመርኃግብሩም በትኬት ሽያጭ፣ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችን በመጫረት እና ቀጥተኛ ድጋፍ በማድረግ ከ75 ሽህ ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
በኒውዮርክ የኢፌዴሪ ምክትል ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ መንግሥት ባለፉት ሦስት ዓመታት እየወሰደ ካለው የለውጥ እርምጃ በተቃራኒ የቆሙ የውስጥና የውጭ ጸረ-ሰላም ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ስጋት መደቀኑን ተናግረዋል።
በአማራ ክልል አጣዬና ከሚሴ አካባቢ በነበረው የጸጥታ ችግር ወገኖች ላይ የተፈፀሙ ጥቃቶችም ለረጅም ዘመናት ተዋልደውና ተሳስበው የሚኖሩ ወንድማማች ሕዝቦችን በማጋጨት ግባቸውን ለማሳካት ያደረጉት ጥረት አካል መሆኑንም አንስተዋል። በክስተቱም የበርካታ ወገኖች ሕይወት መጥፋቱን፣ ንብረት መውደሙን፣ በርካቶች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በአሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መውደቃቸውን በማውሳት የቴክኒክ ኮሚቴው አጥንቶ ያቀረበውን የጉዳት መጠን ገልጸዋል።
በኒውዮርክና አካባቢው የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ከዚህ በፊት ለተለያዩ ሀገራዊ ጥሪዎች ፈጥኖ በመድረስ ሲያደርጉት የነበረውን ርብርብ በማድነቅ ምስጋና አቅርበዋል።
የደረሰው ጥቃት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመ ጥቃት መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር በመረባረብ የወገኖቹን ህይወት ለመታደግ የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣይ ተጨማሪ ገንዘብ ለማሰባሰብ እንደሚሠራም ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበጣና ሃይቅ ላይ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችን ጀልባ መሰወር ተከትሎ ፖሊስ ተሳፋሪዎችን ለማግኘት የተጠናከረ አሰሳ እያደረገ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡
Next articleወጣቶች ከ’ሀውጃኖ’ ምን ይማራሉ?