
አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የሚሊሻ ኀይል አባላት ገለጹ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የሚገኙ የሚሊሻ ኀይል አባላት የአማራ ሕዝብ በአሸባሪው ትህነግ ቡድን ይደርስበት የነበረውን ግፍና በደል ለማስቀረት ሲታገሉ መቆየታቸውን አንስተዋል። አሸባሪውን ቡድን ከመከላከል ባለፈ ጨርሶ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
የሚሊሻ አባል አወቀ ባዜ አባቶች ሕይወታቸውን ሰጥተው፣ ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ያቆዩአትን ሀገር ከአሸባሪው ትህነግ ለመጠበቅ ቡድኑን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ መዘጋጀቱን ገልጿል።
ሌላው የሚሊሻ አባል ብዙነህ ጨቅሌ አሸባሪው ትህነግን በገባበት ጉድጓድ ገብተው ለመደምሰስ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።
የእናት ጡት ነካሹ የትህነግ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መቀበር አለበት ያሉት ደግሞ የሚሊሻ አባል መሠረት ቀለብ ናቸው፡፡
የሚሊሻ አባላቱ ወቅቱ የአሸባሪውን ትህነግን እኩይ ሴራ የሚያመክኑበት ብቻም ሳይሆን ዳግም እንዳይፈጠር የማድረግ ሥራ የሚሠራበት እንደሆነ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ደሴ- ከአዳኝ አገር ጫቆ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ