“አረሙ እንዲነቀል አድርገን እንሠራለን። አረሙን ስንነቅል ግን ስንዴውን እንዳንጎዳው የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

271

“አረሙ እንዲነቀል አድርገን እንሠራለን። አረሙን ስንነቅል ግን ስንዴውን እንዳንጎዳው የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት
አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል፡፡
የገጠምነው ጠላት የኢትዮጵያ ነቀርሳ የሆነውን ጠላት ነው። ጁንታው ያገኘውን የፖለቲካ ሥልጣን የገዛ ሀገሩን ለማፍረስ
የተጠቀመ ምናልባት በታሪክ ብቸኛው ቡድን ነው። አብሮ የኖረ ሰይጣን በቶሎ አይነቀልም እንደሚባለው በግራ በቀኝ
መፍጨርጨሩ አይቀርም።
በርግጠኝነት ግን ጁንታው መልሶ እንዳይበቅል ሆኖ ይነቀላል።
ይህ የሚሆነው ሁላችንም እንቦጩን ለመንቀል ከተረባረብን ነው። በሂደቱ ውስጥ እዚህና እዚያ ግለሰቦች ሊሳሳቱ ይችላሉ።
ሐሳብ የሚከፋፍሉ መረጃዎች ሊሰሙ ይችላሉ። በግብ አንድ ሆነን የአካሄድ ክርክር ይፈጠር ይሆናል።
ያም ሆነ ይህ ከግባችን አያናጥበንም። የኢትዮጵያ ልጆች ከአራቱም ማዕዘን የጁንታውን ዕቅድ ለመቀልበስ ተነሥተዋል። ይህ
በራሱ ድል ነው። የኢትዮጵያ ልጆች ጠላታቸው ማን እንደሆነ ለይተውታል። እርሱንም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ዐውቀዋል።
ያንንም ያደርጉታል።
ይህ አንድነታችን ያስፈራቸው ኃይሎች የሚከፋፍል የመሰላቸውን ነገር ሁሉ ያደርጋሉ። ዓይነ መዓታችንን ከእነርሱ ላይ አንሥተን
በገዛ ወገኖቻችን ላይ እንድንተክል ያሤራሉ። ፈጽሞ አናደርገውም።
አሁን የፈጠርነው አንድነት የጁንታውን የጥንት ሤራ ያፈረሰ፤ ቀጥሎም የሤራውን ባለቤት የሚያፈርስ፤ በመጨረሻም የተሤረባትን
ሀገር በአንድነት የሚያድስ ነው።
መከላከያ ኃይላችንና የክልል ኃይሎቻችን ተገቢውን ቦታ እየያዙ ነው። ያንን ለማወክ ትንኮሳ ይኖራል። ለዚያ ለራሳችን ቃል
የገባነውን የተኩስ አቁም እያከበርን ተገቢውን ምላሽ ይሰጠዋል።
ምንን፣ ለምን፣ እንዴት፣ የትና መቼ ማድረግ እንዳለብን ጥብቅ ዕቅድ አለን። ውጤቱን በጥቂት ጊዜ ውስጥ ወዳጅም ጠላትም
ያየዋል። ሠራዊታችን አስፈላጊ ሲሆን እጅን በአፍ ላይ ለሚያስጭን ተልዕኮ ተዘጋጅቷል።
አረሙ እንዲነቀል አድርገን እንሠራለን። አረሙን ስንነቅል ግን ስንዴውን እንዳንጎዳው የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን።
በሀገራችን አረም በደቦ ነው የሚነቀለው። የኢትዮጵያ ልጆችም እርሱን እያደረጉት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት መጠናከር በሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ ትብብርና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡
Next article“ለአማራ ሕዝብ ስንል የምንከፍለው ማንኛውም ዓይነት መስዋዕትነት ለኛ ቢያንስ እንጂ አይበዛም” የአማራ ልዩ ኀይል 29ኛ ጣና ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ አባላት