የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት መጠናከር በሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ ትብብርና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡

99

የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት መጠናከር በሀገራቱ ኢኮኖሚያዊ ትብብርና ዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ
ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት መጠናከር ከሕዝብ ለሕዝብ
ግንኙነት ባለፈ ለኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከርና መስፋፋት እንዲሁም በዲፕሎማሲ ግንኙነቱም ላይ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው
ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑክ ሃይማኖት ለሰላም እና አብሮነት መጠናከር ያለውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር ዓላማ
ያደረገ የሥራ ጉብኝት በኬንያ ናይሮቢ እያካሄደ ይገኛል።
ልዑኩ ከኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከአፍሪካ የሃይማኖት መሪዎች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብአባላትና በኬንያ
ከኢትዮጵያ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ጋር ወይይት ማድረጉን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ታጋይ
ታደለ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ እና የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤዎች በቀጣይ በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በመለየት ትብብራቸውን
በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ተወያይተዋል፡፡ በቀጣይ የጋራ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም እንደሚሠሩ በውይይቱ ማረጋገጣቸውን
ተናግረዋል።
በሌላ መልኩ የጉባኤው ጸሐፊ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ የኬንያ መንግሥት ኢትዮጵያ እየገነባች ያለውን
የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ እና ከእውነት ጎን በመቆም ላሳየችው ቁርጠኝነት እና ለሰጠችው ድጋፍ በጉባኤው ስም
አመስግነዋል።
የኬንያ የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ ቢሾፕ ጆሴፍ ማታው “የሁለቱ የሃይማኖት ተቋማት ግንኙነት መጠናከር ከሕዝብ ለሕዝብ
ግንኙነት ባለፈ ለኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከርና መስፋፋት የጎላ ድርሻ ይኖረዋል” ብለዋል።
በሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይም ወሳኝ ሚና ይጫወታል በማለት ገልጸዋል።
የአባይን ግድብ በተመለከተ “ኢትዮጵያ በራስዋ ሀብት የመልማት ፍላጎት ትክክለኛ እና ተገቢ መሆኑን ገልጸው ድጋፋቸውን
እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በናይሮቢ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ቅርንጫፍ ለመመስረት አደራጅ ኮሚቴ መሰየሙም
ተነግሯል፡፡ ኢዜአ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየደብረብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
Next article“አረሙ እንዲነቀል አድርገን እንሠራለን። አረሙን ስንነቅል ግን ስንዴውን እንዳንጎዳው የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ