የሀገር ጠላትን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን የሰቲት ሑመራ ከተማ ሴቶች ገለጹ።

371
የሀገር ጠላትን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውን የሰቲት ሑመራ ከተማ ሴቶች ገለጹ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ ሴት፣ ወንድ፣ ህፃንና አዛውንት ሳይል ለሰላሳ ዓመታት በኢትዮጵያና በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ ግፍና መከራን ሲያደርስ እንደነበር የሑመራ ከተማ ሴቶች ተናግረዋል።
ይህ ሀገር አፋራሽ አሸባሪ ቡድን በማይካድራ ንፁሃንን በመጨፍጨፍ ሰው በላነቱን አሳይቷል ብለዋል። የሀገር ጠላት የሆነውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ በተጠንቀቅ ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪ ትዕግሥት ተገኘ “በዚህ የህልውና ዘመቻ ላይ ለመሳተፍ በተጠንቀቅ ላይ ነን፤ ለልዩ ኀይላችን ለሚሊሻ አባላት ስንቅ በማዘጋጀት አለፍ ሲልም ጦር ግንባር በመዝመት የሚጠበቅብንን ኀላፊነት ለመወጣት በተጠንቀቅ ላይ እንገኛለን” ብላለች።
“ዘመቻውን ለመቀላቀል ሴትነቴ አያግደኝም” ያለችው ደግሞ ሌላዋ የሰቲት ሁመራ ከተማ ነዋሪ ሃይማኖት ገብሩ ናት። ሃይማኖት ገብሩ እናቶቻችን ጦር ሜዳ በመዝመት አኩሪ ታሪክን አስመዝግበዋል፤ ሴትነት የጥንካሬ መገለጫ ነው፤ ሀገር አፍራሹን የትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ እና ሀገርን ለማዳን የህልውና ዘመቻውን ተቀብለን በተጠንቀቅ ላይ እንገኛለን ነው ያለችው።
“ሀገር የህልውናችን መሠረት ናት፤ ሀገር ስትፈርስ ማንም ዳር ላይ ኾኖ አይመለከትም፤ ይህን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ቆርጠን በመነሳት በተጠንቀቅ ላይ እንገኛለን” ብለዋል የሑመራ ከተማ ሴቶች።
ዘጋቢ:– ያየህ ፈንቴ–ከሑመራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየጎንደር ከተማ ሚሊሻ አባላት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እና ዘመቻ ለህልውና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።
Next articleየአሸባሪውን ትህነግ የመጨረሻ አስትንፋስ ለማቋረጥ ሁሉም በጋራ እንዲቆም የአፋር ክልል መንግሥት ጥሪ አቀረበ፡፡