የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ።

393
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 476 የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ።
ሠልጣኞቹም በፖሊሰ ሳይንስ፣ በሥነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትሕ፣ በነርሲንግ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ዩንቨርስቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችንም አስመርቋል።
በየትምህርት ዘርፉ የላቀ ውጤት ላመጡ ተመራቂ መኮንኖች ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ዩንቨርስቲው ከተቋቋመ 74 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በቅርቡም ከኮሌጅ ወደ ዩንቨርስቲ ማደጉ ይታወሳል።
በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተካሄደ የምርቃት ሥነ-ሰርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች መገኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleተመራቂዎች በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ለሚያጋጥማችው ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኜ (ዶክተር) አስገነዘቡ፡፡
Next articleየጎንደር ከተማ ሚሊሻ አባላት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እና ዘመቻ ለህልውና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ።