ተመራቂዎች በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ለሚያጋጥማችው ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኜ (ዶክተር) አስገነዘቡ፡፡

204
ተመራቂዎች በትምህርት ያገኙትን ዕውቀት በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ለሚያጋጥማችው ችግር መፍቻ ቁልፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኜ (ዶክተር) አስገነዘቡ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2 ሺህ 363 ተማሪዎች ዛሬ ተመርቀዋል፡፡ ከተመራቂዎች ውስጥ 32 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። ዩኒቨርሲቲው በመደበኛና በሌሎች የትምህርት መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በኹለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ እና በስፔሻሊቲ ሕክምና ነው ያስመረቀው፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኜ (ዶክተር) ተመራቂዎች በትምህርት ያገኙትን እውቀት በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ለሚያጋጥማችው ችግር መፍቻ ቁልፍ በማድረግ በአሸናፊነት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተመራቂዎች ማኅበረሰቡን በቅንነት በማገልገል የሚጣልባቸውን ኀላፊነት በብቃት እንዲወጡም አደራ ብለዋል፡፡
በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ለሀገር ግንባታ እንዲጠቀሙበት አስገንዝበዋል።
“ለቀጣይ የልህቀት ጉዟችሁ ስንቅ ይዛችሁ ወጥታችኋል፤ ይህን በዘመናችሁ ሁሉ በመጠቀም ሀገራችሁን አገልግሉበት ብለዋል” ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህጻናትን በሀሽሽ አዕምሯቸውን አደንዝዞ ወደ ጦርነት እየማገደ መሆኑን ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ።
Next articleየኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ በተለያዩ መረሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ።