
“ኢትዮጵያዊነትን ማጠናከርና ፈጣሪን መፍራት ለሀገራችን ትልቁ መፍትሔ ነው” ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ለመላ ሕዝበ ሙስሊሙ ለአረፋ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአረፋ በዓልን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ኢትዮጵያ ሰላማዊ ምርጫ ማካሄዷም ትልቅ ደስታ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይ መንግሥት የሚመሠርተው ፓርቲም ሀገርና ሕዝብን አንድ አድርጎ ማስተዳደርና በዘርና ሃይማኖት መከፋፈልን፣ አጉል ቅራኔንና መገፋፋትን ማስቆም ይኖርበታል ብለዋል።
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊያን መገንዘብ ያለባቸው በህዳሴ ግድብ ያሉ ችግሮችንም በጋራ መፍታትና የውኃ ሙሌቱን በመተባበር መከወን ነው ብለዋል።
በዓለም ላይ የተከሰተውን የኮሮናሻይረስ ወረርሽኝም ፈጣሪ እስኪያጠፋው ድረስ መከላከያ መንገዶችን መከተል ይገባናል ነው ያሉት።
“ከሁሉ በላይ ግን ኢትዮጵያዊነትን ማጠናከርና ፈጣሪን መፍራት ለሀገራችን ትልቁ መፍትሔ ነው” ብለዋል ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ በመግለጫቸው።
ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ