
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛው ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ እና የሥራ ዘመን ማጠቃለያ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ ለጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ያለውን ክብር በመግለጽ በሕመም በሞት የተለዩ የምክር ቤቱን አባላትንም አስቧል።
የምክር ቤቱን ጉባኤ ያስጀመሩት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ዘርፈሽዋል ንጉሤ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ እና አሳታፊ ምርጫ በማካሄድ በበርካታ ጫና ውስጥ ሆና አሸናፊ በሆነችበት ማግስት እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ታሪካዊ ያሰኘዋል ብለዋል።
አሸባሪው ትህነግ ለትግራይ ሕዝብ ሲባል በብልህ የአመራር ጥበብ የተደረሰበትን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሕፃናትን አሰልፎ ኢትዮጵያ ላይ የከፈተው ጦርነት እና የውጭ ኃይሎች ጫና ደግሞ ፈተናዎች መሆናቸውን አፈጉባኤዋ አንስተዋል።
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጀት ዓመቱን የማጠቃለያ ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የከተማ አስተዳደሩ የኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት እንደሚቀርብ እና ምክር ቤቱ የ2014 በጀት ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ዘገባው የኢብኮ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ