ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸዉን የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።

192
ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸዉን የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፓሬሽን ያነጋገራቸዉ የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሸብርተኛው ትህነግ ትንኮሳ መጀመሩን ተከትሎ በመደራጀት የአካባቢያቸዉን ሰላም በተጠንቀቅ እየጠበቁ ይገኛሉ።
ወደ ግዳጅ ቀጣና ለተሰማራዉ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ስንቅ እያቀረቡ ሲሆን በቀጣይም የሕይወት መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸዉንም ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል።
የአዲአርቃይ ከተማ እናቶች በበኩላቸዉ ለዘማቾች ስንቅ በማዘጋጀትና በማቅረብ ሰፊ ሥራ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።
“ሽብርተኛውን ትህነግ ለማጥፋት የማንከፍለዉ ዋጋ የለም” ነው ያሉት።
የአዲአርቃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ መልኬ እንደነገሩን የወረዳዉ ሕዝብ ለዘመቻዉ እያደረገ ያለዉ ድጋፍ ሰፊ መሆኑን ገልጸዉ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ የወረዳው ሕዝብ ሽብርተኛውን ትህነግ ከአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ለመደምሰስ ዝግጁ ነዉ ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ይርጉ ፋንታ-ከአዲአርቃይ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ክልሎች ልዩ ኀይሎቻቸውን እና ሚሊሻዎቻቸውን ቢያዘምቱ የሚገርም አይደለም” አምባሳደር ኽርማን ኮህን “በትግራይ ክልል ህጻናት ወደ ጦርነት መሰማራታቸውን ዓለም በጥብቅ ሊያወግዝ ይገባል” ፕሮፌሰር አን ፊዝ ጄራልድ
Next articleየተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።