አምኒስቲ ኢንትርናሽናል በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ መንግሥትን ለመወንጀል የተጠቀመበት ፎቶ የሀሰት መሆኑ ተጋለጠ።

224
አምኒስቲ ኢንትርናሽናል በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጆችን በተመለከተ መንግሥትን ለመወንጀል የተጠቀመበት ፎቶ የሀሰት መሆኑ ተጋለጠ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ የሆነው አማኑኤል ስለሺ በቲውተር ገፁ እንዳስታወቀው፤ ፎቶው በኢትዮጵያ በተካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመሩ መራጮች በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ ሲደረግላቸው የሚያሳይ ነው ብሏል።
ይህን ፎቶ ግራፍ እኔ ለአጃስ ፍራንስ ፕሬስ ያነሳሁት ነው ያለው ጋዜጠኛው፤ አምኒስቲ ኢንትርናሽል በተሳሳተ መንገድ መጠቀሙ እንዳሳዘነው ጠቅሷል።
ድርጊቱ ከሙያ ሥነ-ምግባር ያፈነገጠና ስህተት ነው ሲል የገለፀው አማኑኤል ተቋሙ ፎቶ ግራፉን እንዲያነሳው ጠይቋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ኢትዮጵያን በሀሰት መረጃዎችን ለመወንጀል እየተንቀሳቀሱ ነው።
አምንስቲ በትግራይ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ እና በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደርሰው ግድያ እና አፈናን በተመለከተ እስካሁን ያለው ነገር አለመኖሩ የድርጅቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የጣለ ሌላ አጋጣሚ ሆኗል ነው ያለው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‹‹የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በፍጹም ጀግንነትና በሙሉ ፈቃደኝነት ሀገራዊ ግዳጁን ተቀላቅለዋል›› አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት
Next article“ክልሎች ልዩ ኀይሎቻቸውን እና ሚሊሻዎቻቸውን ቢያዘምቱ የሚገርም አይደለም” አምባሳደር ኽርማን ኮህን “በትግራይ ክልል ህጻናት ወደ ጦርነት መሰማራታቸውን ዓለም በጥብቅ ሊያወግዝ ይገባል” ፕሮፌሰር አን ፊዝ ጄራልድ