
‹‹የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በፍጹም ጀግንነትና በሙሉ ፈቃደኝነት ሀገራዊ ግዳጁን ተቀላቅለዋል››
አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባሎች በፍጹም ጀግንነትና በሙሉ ፈቃደኝነት አገራዊ ግዳጁን መቀላቀላቸውን የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ አስታወቁ፡፡
መከላከያ ሠራዊቱን በሞራልም ሆነ በስንቅ መደገፍ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ አቶ ደስታ ሌዳሞ በተለይ እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው ትህነግ በባህሪው በሰላም ውስጥ መኖር የሚችል ድርጅት አይደለም፡፡ የህዝብን መሠረታዊ ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ ሲያቅተው ትኩረት ለማስቀየስ ሲል ግጭቶች ውስጥ ይገባል፡፡
ግጭቶችንም ህዝባዊ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ ይህ የቆየ ባህሪው ነው ፣ ወደፊትም ለተወሰነ ጊዜ በዚሁ ሊቀጥል ይችላል፡፡
የሀገርን ሰላም ለመጠበቅ በሚደረገው ትግል ውስጥ የመከላከያ ሠራዊታችን ግንባር ቀደም እንደመሆኑ ሁሉን አቀፍ እገዛ ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ደስታ፣ ከክልሉ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በተደረገ ውይይት የተንጸባረቀው መከላከያ ሠራዊትን በሞራልም ሆነ በስንቅ የመደገፍ መነሳሳት ነው ብለዋል፡፡
የጁንታውን ጥጋብ ለማስታገስ ጀግናው የመከላከለያ ሠራዊታችን በግንባር ቀደምትነት ተሰልፎ ይገኛል፡፡
ይህን የመከላከያ ሠራዊታችንን በሰው ኃይል፣ በሞራል እንዲሁም በትጥቅና ስንቅ ማጠናከር ይጠበቅብናል፡፡ ህዝቡ ለሠራዊቱ ተገንነቱን ብሎም ደጀንነቱን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል ።ኢትዮጵያ ሰፊ ብሎም ትልቅ አገር ስለሆነች ሁላችንም ዳር እስከ ዳር በመነቃነቅ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማሟላት እንችላለን ብለዋል፡፡ ኢፕድ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ