የማይካድራ ከተማ ወጣቶች የአሸባሪው ትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

134
የማይካድራ ከተማ ወጣቶች የአሸባሪው ትህነግ ቡድንን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራ ሕዝብ ላይ ካሳረፈው የጥላቻ በትር አንዱ በማይካድራ ወገኖች ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ ይጠቀሳል፡፡አሸባሪው የትህነግ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን የህልውና ፈተና መመከት በሚቻልበት ዙሪያ የከተማው ወጣቶች ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አሸባሪውን የትህነግ ቡድንን ለማስወገድ ዝግጁ መሆናቸውን ወጣቶች ገልጸዋል፡፡
ለአሸባሪው ቡድን የሚሠሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድም ጠይቀዋል፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ሀብታሙ አለልኝ በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ወጣቶችን የማደራጀት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ የተሰገሰጉ የጠላት ኀይሎችን ለማጥራት በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ወጣቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወንድሞች ጋር የጋራ ጠላት የሆነውን አሸባሪው ትህነግ እንዲመክቱ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፋኖስ በየነ ወጣቶች ያሳዩት ተነሳሽነት ከአያት ቅድመ አያቶቻቸው የወረሱት ወኔ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ የማደራጀት ሥራው ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
በውይይቱ የማይካድራ ከተማ ወጣቶች፣ የዞኑና የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ-ከማይካድራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleሁሉም ኢትዮጵያዊ ለኢትዮጵያ ኀልውና በአርበኝነት መንፈስ እንዲነሳ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ጥሪ አቀረበ፡፡
Next articleየድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ሕግን ለማስከበር ተልዕኮ ምላሽ ሰጠ፡፡