
“ሕዝባችንን እና አካባቢያችንን ለመታደግ የሕልውና ዘመቻ ላይ ነን፤ ተጨማሪ ኃይልም ወደ ድንበር እያስጠጋን ነው” ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ
ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶክተር) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ አሸባሪው ቡድን ትህነግ በድንበር አካባቢዎች ትንኮሳ መፈጸሙን በመግለጽ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት እና ሚሊሻ ወደ አካባቢዎቹ ዘልቆ በመግባት የተቃጣውን ወረራ እየመከቱ ነው ብለዋል፡፡
የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት ከአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ (ዶክተር) ጋር ቆይታ ያደረገው አልጀዚራ “የክልሉን ሕዝብና አካባቢውን ከወራሪው ቡድን ለመከላከል ተጨማሪ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ወደ ድንበር ዘልቆ እየገባ ነው” ብለዋል ይላል፡፡
አሸባሪው ትህነግ በፌደራል መንግሥት የተወሰነውን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ በኢትዮጵያ ላይ ግልጽ የህልውና ስጋት ደቅኗል ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ “ሕዝባችንን እና አካባቢያችንን ለመታደግ የሕልውና ዘመቻ ላይ ነን፤ ተጨማሪ ኃይልም ወደ ድንበር እያስጠጋን ነው” ብለዋል፡፡
ኃይላችንን አንድ ኢንች ወደ ትግራይ ክልል አናስገባም ነገር ግን ሕዝባችንን እንጠብቃለን ነው ያሉት ዶክተር ፋንታ፡፡
አሸባው ትህነግ በተለያዩ የክልላችን አካባቢዎች የከፈተውን ጥቃት እየተከላከልን ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ለዚህም ሕዝቡ ራሱን እንዲከላከል ጥሪ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡
በታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ