
ሁሉም የብዙኃን መገናኛ ተቋማት የጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ ምግባርን ተከትለው እንዲሠሩ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ጥሪ አቀረበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን አዋጅ ተላልፏል ያለውን አዲስ ስታንዳርድ ኦንላይን ሚዲያን ማገዱን አስታውቋል፡፡
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በይፋዊ ማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው አዲስ ስታንዳርድ ኦንላይን ሚዲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወጣውን አዋጅ በመተላለፉ ጊዜአዊ እገዳ ተጥሎበታል፡፡
አዲስ ስታንዳርድ ኦንላይን ሚዲያ ጊዜያዊ እገዳው የተላለፈበት በባለስልጣኑ የክትትል ግኝቶች ፣ ቅሬታዎች እና ከሽብርተኛው ትህነግ ጋር ያለውን ግንኙነት ተከትሎ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡
በእነዚህ እና በሌሎች ተዛማጅ የሥነ ምግባር ጉድለቶች ጥልቅ ምርመራ የሚደረግ መሆኑን የጠቀሰው ባለሥልጣኑ ተጨማሪ እርምጃዎች ሊወሰድበት እንደሚችልም አስታውቋል፡፡
ሁሉም የብዙኃን መገናኛ ተቋማት የጋዜጠኝነት ሙያ ሥነ ምግባርን ተከትለው እና የሕግ የበላይነትን አክብረው እንዲሠሩም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ባለስልጣኑ የፕረስ ነፃነት ከተጠያቂነት ጋር መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል ብሏል፡፡
በየማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ