የትህነግ አሸባሪ ቡድን ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ገለጹ።

229
የትህነግ አሸባሪ ቡድን ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ገለጹ።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትህነግ አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የጀመረውን ጦርነት ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ገለጹ።
ወጣቶቹ አሸባሪው የትህነግ ቡድን የመንግሥትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ባለመቀበል እየፈጸመ ያለውን የሽብር ተግባር እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል።
ወጣት ኦባንግ ኮመዳን እንዳለችው፤ አሸባሪው ቡድን በትግራይና አጎራባች ክልሎች እያካሄደ ያለው የሽብር ወንጀል የሚያሳፍር ነው።
አሸባሪው ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገውን እኩይ ተግባር ለመቀልበስ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኹሉ የዜግነት ግዴታዋን ለመወጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች።
የጥፋት ቡድኑ ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ሳያንሰው አሁን ተጨማሪ ጥፋት እያደረሰ መሆኑን የገለጸው ደግሞ ወጣት ኃይሌ አራጌ ነው።
ባለፈው ጥቅምት ወር በሀገር መከለካያ ሠራዊት ላይ ከፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በማይካድራና ሌሎች አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ተጨማሪ ጉዳት ማድረሱን እንደቀጠለበት ተናግሯል።
ቡድኑ በሕዝቡ ላይ የሚፈጽመውን ጥቃትና ሀገር የማፍረስ ዓላማውን ለማክሸፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአንድነት እንዲነሱ መልዕክት አስተላልፏል።
ወጣት ኮንግ ጋድቤል በበኩሉ፤ አሸባሪው ቡድን ከ20 ዓመታት በላይ የትግራይ ሕዝብና ድንበርን ሲጠብቅ የቆየውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ያጠቃ ከሃዲ መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን ኮንኗል።
ሀገር ለመበታተን የመጣን ኃይል ቁጭ ብሎ እንደማያይ የገለጸው ወጣቱ፤ ከመንግሥት ጎን በመሆን የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት መዘጋጀቱን ነው የተናገረው።
ኢትዮጵያን አፍርሳለሁ ብሎ የተነሳውን ኃይል ለመመከት ኢትዮጵያዊያን መነሳት አለብን ብሏል። ኢዜአ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር እስከ ህይዎት መስዋእትነት የደረሰ ግዳጅ ለመፈጸም ተዘጋጅተናል” የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች
Next article“ሀገር ለማፍረስ የመጣን ኃይል በሕብረት ከመታገል ውጪ ምንም አማራጭ የለም›› የሱማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ