“ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር እስከ ህይዎት መስዋእትነት የደረሰ ግዳጅ ለመፈጸም ተዘጋጅተናል” የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች

160
“ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር እስከ ህይዎት መስዋእትነት የደረሰ ግዳጅ ለመፈጸም ተዘጋጅተናል” የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች
ባሕር ዳር: ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያ ያሳለፈችውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ሀገሪቱን ለመበታተን ቆርጦ ተነስቷል። ይህንም እኩይ ድርጊቱን ለመፈጸም በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአማራ ሕዝብ አሸባሪው ትህነግ የከፈተው ጦርነት የህልውና ጉዳይ መሆኑን ተረድቶ በተለያየ አቅጣጫ እየመከተ ይገኛል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር በወቅታዊ ሁኔታና ለህልውና ዘመቻ ግንባር ላይ ለተሰለፉ የጸጥታ ኀይሎች በሚደረገው ድጋፍ ላይ የመንግሥት ሠራተኛው ሚናን በሚመለከት ወይይት አካሂዷል።
ወይዘሮ ሀገኘሁ ውብነህ በምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያ ናቸው። አሸባሪው ትህነግ የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል፤ ይህንን ለመመከት ደግሞ እስከ ህይዎት መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ነው የገለጹት። አሁን ላይ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለህልውና ዘመቻ ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል። በቀጣይም በሁሉም ድጋፎች ለመሳተፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዞኑ ትምህርት መምሪያ ባለሙያ አቶ አበባው ከበደ የአሸባሪው ትህነግ አማራን የማጥፋት ሴራ አሁን ብቻ ሳይሆን ገና በርሃ እያለ በማንፌስቶው አጀንዳ አድርጎ ሲሠራበት የቆዬ ነው ብለዋል።
ካሁን ቀደም የነበራቸውን የውትድርና ሙያ በመጠቀም ትህነግን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
መላው ኢትዮጵያዊም ይህንን ሀገር አፍራሽ የሆነ ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው የህልውና ዘመቻ ሊሳተፍ ይገባል ነው ያሉት።
አቶ አበባው የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለህልውና ዘመቻው ለመስጠት መወሰናቸውን ተናግረዋል።
የዞኑ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የጤና መምሪያ ኀላፊ አቶ ወንድሜነህ ልየው አስተዳደሩ ሰላም አስከባሪ ኀይል ከማሠማራት ባሻገር ለጸጥታ ኀይሉ የሚውል ሎጀስቲክ 456 ሚሊዮን ሃብት በጥሬ ገንዘብና በአይነት ለመሰብሰብ አቅዶ እየሠራ ነው ብለዋል።
ከሥራ ኀላፊዎችና ከመንግሥት ሠራተኛው ጋር በተደረገ ውይይት ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ የአንድ ወር ደሞዝን ለመስጠት መወሰኑንም ገልጸዋል።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ለህልውና ዘመቻ ድጋፍ የሚውል እስካሁን 6 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሃብት በጥሬ ገንዘብና በአይነት መሠብሰቡን አስተዳደሩ አስታውቋል።
ዘጋቢ:- ዘመኑ ይርጋ – ከፍኖተሰላም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበዋግ ኽምራ ግንባር የተሰለፉ የአማራ ሚሊሻ አባላት አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገለጹ።
Next articleየትህነግ አሸባሪ ቡድን ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶች ገለጹ።