አሸባሪውን ትህነግ መከላከል ብቻ ሳይሆን ማስወገድ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የጸጥታ አማካሪ ገለጹ።

123
አሸባሪውን ትህነግ መከላከል ብቻ ሳይሆን ማስወገድ እንደሚገባ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የጸጥታ አማካሪ ገለጹ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 09/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ዝክረ ሐምሌ አምስት የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የወልቃይት ወጣቶች በተገኙበት በሑመራ ከተማ ትናንት ታስቦ ውሏል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው በአሸባሪው ትህነግ በሠራዊቱ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ አንስቶ የተስተዋሉ ተያያዥ ችግሮችን ለወጣቶቹ አብራርተዋል።
አሸባሪው ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚሰነዝረውን ትንኮሳ ለመጨረሻ ጊዜ ለመቋጨት እየተሠራ እንደሆነም አቶ አሸተ አንስተዋል።
በምክትል ቢሮ ኀላፊ ማዕረግ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የጸጥታ ጉዳዮች አማካሪ ከፋለ እሱባለው ሕዝቡ ንቁ ሠራዊት በመሆን በሕልውናው ላይ የመጣውን ፈተና በድል ለመወጣት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የውጭና የውስጥ ኀይሎች ኢትዮጵያን ለማዳከም ጋብቻ መፈጸማቸውን ያነሱት አማካሪው የውጭ ኀይሎች በሁሉም ዘርፍ ደካማ ኢትዮጵያን የመፍጠር ዓላማ ይዘው እየሠሩ እንደሆነ አማካሪው ተናግረዋል።
አሸባሪው ትህነግ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንዳትኖር አልሞ እየሠራ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።
የሽብር ቡድኑ እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ አማራ ክልልን ዋጋ ስለሚያስከፍል ጦርነቱን በፍጥነት መቋጨትና ወደ ሌሎች የልማት ሥራዎች መሰማራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የአሸባሪውን ትህነግ ቡድን አባላት መከላከል ሳይሆን ማስወገድ ይገባልም ብለዋል።
ለዚህም የሚያጋጥም ፈተናን በቁርጠኝነት ለመጋፈጥ መዘጋጀት እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ ወጣቶች ሲደርስባቸው ከነበረው ግፍና በደል ነጻ መውጣታቸውን አንስተዋል።
አሸባሪውን ትህነግ ለማጥፋት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ-ከሑመራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል እውቀት ግንባታ ላይ በትኩረት እንዲሠሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጠየቀ።
Next articleበዋግ ኽምራ ግንባር የተሰለፉ የአማራ ሚሊሻ አባላት አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገለጹ።