በአማራ ክልል ሰላማዊ ሰልፎቹ በሰላም ተጠናቅቀዋል፡፡

315

ባሕር ዳር፡ መስከረም 11/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና በምዕመኗ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን በመቃወም ዛሬ በአማራ ክልል ሰልፎች ተካሂደው በሠላም ተጠናቅቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ እንዲቆም፣ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት አካላትም በሕግ እንዲጠየቁ ነው በተለያዩ ከተሞች በተካሄዱ ሰልፎች ምዕመናኑ እና የሀይማኖት አባቶች የጠየቁት፡፡

መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሠጠው፣ በቤተ ክርስቲያኗ እና ምዕምኖቿ ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላትንም ተጠያቂ እንዲያደርግ በሰልፎቹ ተጠይቋል፡፡

ጥቃት የደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናት እንዲሰሩ እና ለተጎዱ ወገኖችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈልም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ሰልፎቹ በባሕር ዳር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በብቸና፣ በደጀን፣ በሞጣ፣ በደብረ ብርሃን፣ በማጀቴ፣ በጫጫ፣ በአረርቲ፣ በመሐል ሜዳ፣ በፍኖተ ሠላም፣ በቡሬ፣ በመርዓዊ፣ በደባርቅ፣ በዳባት፣ በአዲ አርቃይ፣ በጯሂት፣ በወልድያ፣ በላልይበላ፣ በውጫሌ፣ በጋዞ ወረዳ፣ በአይና ቡግና ወረዳ፣ በመርሳ፣ በራያ ቆቦ፣ በወረኢሉ፣ በደላንታ፣ በዋድላ፣ በዳንግላ፣ በዱር ቤቴ፣ በአዲስ ዘመን እና በሌሎችም ከተሞች ተካሂደዋል፡፡

የአቋም መግለጫዎችን በማሰማት ሰልፎቹ በሠላም መጠናቀቃቸውንም በየከተሞቹ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችንና ምንጮቻችን መረጃ አድርሰውናል፡፡

ፎቶ፡- ከአብመድ ዘጋቢዎች እና ከማኅበራዊ ድረ ገጽ

Previous article“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የኦሮሞውም፣ የትግራዩም፣ የከንባታውም … የሁሉም ናት::” የባሕር ዳር ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም
Next articleበዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግንባታቸው ለዓመታት ተጓቶ የነበሩት የዓሳ ማቆያ እና ማከፋፈያ ጣቢዎችን ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡