
ባሕር ዳር፡ መስከረም 11/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለአንድ ብሔር መስጠት ተገቢነት እንደሌለው የባሕር ዳር ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም አስገነዘቡ፡፡
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ለአንድ ብሔር የሚሰጡ አካላት አሉ፤ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኗ የኦሮሞውም፣ የትግራዩም፣ የከንባታውም … የሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት” ብለዋል አቡነ አብርሃም ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው የሰልፍ ሥነ ሥርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፡፡ ፖለቲካ ከሐይማኖት ጋር መቀላቀል የለበትም ሲሉም አሳስበዋል፡፡
“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ሁሌም ታስባለች፤ ስለ አንድነቷ ትፀልያለች፤ ታስተምራለች፤…ትመክራለች” ብለዋል አቡነ አብርሃም፡፡
ዘጋቢ፡- ኪሩቤል ተሾመ
ፎቶ፡- በኪሩቤል ተሾመ እና በሀይሉ ማሞ