የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና ስጋት ለመቀልበስ ዝግጁ መሆናቸውን የደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

208

የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የህልውና ስጋት ለመቀልበስ ዝግጁ መሆናቸውን የደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መንግሥት የትግራይ አርሶአደሮች የእርሻ ሥራቸውን እንዲያከናወኑ እና ሕዝቡም የጥሞና ጊዜ እንዲያገኝ በማሰብ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ በማድረግ መከላከያ ሠራዊቱ ትግራይን ለቆ እንዲወጣ መደረጉ ይታወሳል፡፡

አሸባሪው ትህነግ ግን የተኩስ አቁም ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው በአማራ ሕዝብ ላይ ሂሳብ አወራርዳለሁ በማለት የቀደመ ጥላቻውን አሳይቷል፡፡

በአማራ ክልል የተለያዩ ጥቃቶችን በመክፈት የተለመደ የሽብርና የጥፋት ሥራውን ቀጥሏል፡፡ በዚህም የአማራ ክልል መንግሥት በጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ ለነበሩ እና የክልሉ ሕዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ እንዲመክት ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በደባርቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው የመንግሥትን ጥሪ እንደተቀበሉና ሰልጥነውም የትህነግ አሸባሪ ቡድን ለመዋጋት እንደተዘጋጁ ገልጸዋል፡፡

ወጣት መልካሙ እሸቴ የመንግሥትን ጥሪ በመቀበል የተጋረጠውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ዝግጁ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

ወጣቶች ተደራጅተውና ሰልጥነው የተጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ዝግጁ መሆን እንደሚገባም ነው የገለጸው፡፡

ሌላኛዋ ወጣት አብረኸት ግርማይ እንዳለችው የህልውና ጉዳይ ሴት ወንድ አይልም፡፡ አሸባሪው ትህነግ በሴቶች ላይም በደል ሲፈጽም ኖሯል፤ አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ስለሆነም እንደ ሌሎች ጀግና እህቶቼ በግንባር ተሰልፌ ግፈኛውን ኀይል ለመዋጋት ዝግጁ መኾኗን ገልጻለች፡፡

ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ -ከደባርቅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትህነግ አሸባሪ ቡድንን ለመመከት መላው ሕዝብ ያልተቆጠበ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ።
Next article‹‹ለሕልውና ዘመቻ ከወር ደመወዝ በተጨማሪ ደም እንሰጣለን›› የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች