አሸባሪው ትህነግ ጊዜ ከተሰጠው የቀጣናው ስጋት እንደሚሆን አሚኮ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ገለጹ፡፡

202

አሸባሪው ትህነግ ጊዜ ከተሰጠው የቀጣናው ስጋት እንደሚሆን አሚኮ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት
መምህር ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ የደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት
ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ሃሳብ ያለው በሃሳቡ እገዛ ማድረግ እንዳለበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ
ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር በዕውቀቱ ድረስ ተናገሩ፡፡ አሸባሪው ትህነግ በአሁኑ ወቅት የአማራ ሕዝብ ሕይወት
የመኖርና ያለመኖር ዋስትናን አደጋ ላይ ለመጣል እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ባለፉት በርካታ ዓመታት የአማራ ሕዝብን ለማጥፋት በጠላትነት ፈርጆ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ያስታወሱት
የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አደገኝነቱም ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይኾን ለመላው ኢትዮጵያ ነው ብለዋል፡፡
በየትኛውም የዓለም ጫፍ የራሱን የመከላከያ ሠራዊት የወጋ ቡድን በታሪክ ታይቶ አይታወቅም ነው ያሉት፡፡ አሸባሪው ትህነግ ግን
ይህንን መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡
በሶማሊያ፣ ናጄሪያ እና በሌሎች ሀገሮች የሚንቀሰቀሱ አሸባሪዎች እንኳን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ዓለማ ለማሳካት ይሯሯጣሉ
እንጂ ማኅበረሰቡን ለይተው እንዳልወጉም ለአብነት ጠቅሰዋል፤ ሕዝብን ጠላቴ ነው ብለው እንዳልፈረጁም አስረድተዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ግን በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እየፈጸመ የሽብር ተግባሩን ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት የተጋረጠውን የሕልውና አደጋ የሁሉንም ቤት የሚያንኳኳ በመኾኑ ሁሉም ሊታገለው እንደሚገባ
ገልጸዋል፡፡
የሕልውና አደጋውን ለመመከት ደግሞ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ዕውቀት ያለው በዕውቀቱ፣ ሃሳብ ያለው በሃሳቡ እገዛ ማድርግ
አለበት ብለዋል፡፡
በዚህ ታሪካዊ ወቅት እያንዳንዱ ዜጋ ማድረግ የሚችለውን ማድረግ ካልቻለ ሕልናው ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መገንዝብ
ይገባልም ነው ያሉት፡፡
የሕልውና አደጋው ለጊዜው በአማራ ሕዝብ ላይ ብቻ የመጣ ቢመስልም ለኢትዮጵያና ለቀጣናው ሀገራት የተጋረጠ አደጋ
መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ የፌዴራል መንግሥትና ሌሎች ክልሎች ከአማራ ሕዝብ ጎን ተሰልፈው አሸባሪው ትህነግ ላይ
የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸውም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ጦርነት አውዳሚ መኾኑ ይታወቃል የሚሉት የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ይህኛው ግን በግፊት የመጣ
የሕልውና አደጋ በመኾኑ ሕዝቡ ተጠናክሮ አሸባሪ ቡድኑን በማጥፋት ሀገሩን ሊታደግ ይገባል ብለዋል፡፡
የፌዴራል መንግሥቱ የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ገበሬው ተረጋግቶ እርሻውን እንዲያርስ፣ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ለተጎዱ
የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሻለ እገዛ እንዲደረግ እንደነበርም አንስተዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ግን መንግሥት ያደረገውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በመተው የአማራ ሕዝብ ተረጋግቶ የልማት
ሥራውን እንዳይከውን እያደረገ ነው፤ በመኾኑም ሕዝቡ የጋራ ክንዱን በማንሳት ታሪካዊ ጠላቱን ሊፋለም ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የትህነግ ርዝራዦች ኢትዮጵያን ለማዋረድ የሚያደርጉትን ጥረት ለመቀልበስ በቁጭት ተነሳስተናል” አቶ ደስታ ሌዳሞ
Next articleበእርዳታ ስም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የሚገቡ አካላትን መንግሥት እንደማይታገስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡