“በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሠሩ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ የሚያደርግ ሥርዓት ተቋማቱ መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል” ዶክተር አሕመዲን መሐመድ

70
“በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሠሩ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ የሚያደርግ ሥርዓት ተቋማቱ መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል” ዶክተር አሕመዲን መሐመድ
ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀው የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለትምህርት ዘርፉ በሚያደረገው አስተዋጽኦ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) በዩኒቨርሲቲዎችና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሠሩ የፈጠራና የምርምር ሥራዎች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ተቋማቱ ሥርዓት መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ለዚህም በተቋማቱ ውስጥ የሚሠሩ የሥራ ኀላፊዎችና ከተለምዷዊው አመራር ወጥተው ለሥራዎቹ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃን ጨምሮ ዋስትና መስጠት የሚያስችል የአመራር ብሂል መከተል እንደሚኖርባቸው ሐግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ሚኒስትር ዴኤታው በተለያዩ ከፍተኛ ተቋማት ተመራማሪዎችና የቴክኖሎጂ አፍላቂዎች የተከናወኑ ሥራዎችን አውደ ርዕይ ተመልክተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሑመራ ከተማ ዝክረ ሐምሌ 5 እየተከበረ ነው።
Next articleበአንድነት በመቆም በአሸባሪው ትህነግ ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ኮሎኔል አለበል አማረ ገለጹ፡፡