
በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሑመራ ከተማ ዝክረ ሐምሌ 5 እየተከበረ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሐምሌ 5 የአማራ ሕዝብ የነጻነት ተጋድሎ መሠረት ናት። የአማራ ሕዝብን የማንነት ጥያቄ ያነገቡ እንቁዎች ከአፋኙ ትህነግ መራሽ መንግሥታዊ የጭቆና ሥርዓት ጋር ትንቅንቅ የገጠሙበት ቀን ነው። አማራ የጀግንነት ክንዱን ያሳየበት ዕለትም ነው።
የአማራ ሕዝብ የዘመናት ጥያቄ እንዲመለስ ብዙ እህትና ወንድሞች መስዋእት ቢኾኑም የአማራ ሕዝብ የጠላትን አንገት ያስደፋበት እለትም ነበር – ሐምሌ 5።

ሐምሌ 5 የወያኔ የደኅንነት ክፍል የአማራ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ያነገቡትን ጀግኖች የሻቢያ ተላላኪዎች፣ የግንቦት 7 አስፈጻሚዎች፣ ሽፍቶች እና ሌሎች ታርጋዎችን በመለጠፍ በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት አድርጎ የከሸፈበት እለት ነው።
የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴዎችን በድብቅ አፍኖ ለመውሰድ ዘመቻ ተካሂዶ ሳይሳካ የከሸፈበት ታሪክ የሚዘክረው ቀን ነው።
ሐምሌ 5/2008 ዓ.ም ጎንደር ላይ የተለኮሰው ትግል እያደር መቀጣጠል ወደ መላው አማራና ኢትዮጵያ እያደገ ሄዶ ለ27 ዓመት በኢትዮጵያ ላይ የነበረው የጭቆና አገዛዝ ዳግም ላይመለስ ተሰናበተ።
በድል ቀኑ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለአማራ ሚሊሻ እንዲሁም ለፌዴራል ፖሊስ በሕግ ማስከበር ዘመቻው ላስገኙት አንጸባራቂ ድል ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ