”የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል” ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ

212
”የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል” ብርጋዴር ጄኔራል አለማየው ወልዴ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 08/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ የቀጠናውን ሰላም በማስጠበቅ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል” ሲሉ የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት አባል ብርጋዴር ጄኔራል አለማየሁ ወልዴ ገለጹ።
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ተፈጥሮ በነበረ ግጭት ተፈናቅለው በአዊ ዞን ጓንጓ ወረዳ ራች መጠለያ ቆይተው ወደ ዶቢ ቀበሌ መጠለያ ማዕከል የተመለሱ ዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ግዳጅ የተሰጣቸው የአገር መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትን አነጋግረዋል።
እንደ ጄኔራል አለማየው ገለፃ ኮማንድ ፖስቱ ባከናወናቸው ተግባራት በመተከል ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ከ52 ሺህ በላይ ዜጎችን በየወረዳቸው በመመለስ የተመረጡ ማዕከላት እንዲያርፉ ማድረጉን አስታውሰዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትም በየማዕከላቱ እንዲያርፉ የተደረጉ ዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ተግባርም የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በሚያደርጉት አኩሪ ተግባር የመጠለያ ጣቢያዎቹ ከሚገኙ ዜጎች ምስጋና እየተቸረ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ የሆኑት የሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላትም የእከሌ ብሔር ነው ከሚል እሳቤ ነፃ በመሆኑ ህዝብ ሲደሰት ይደሰታል፣ ሲከፋም ያዝናል ብለዋል።
ሠራዊቱ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ በማክሸፍና በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲችልም ሁሉም አባል በስነምግባር የታነጸ በመሆን የተስተካከለ ቁመናን መላበስ እንደሚገባ መክረዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በየወረዳ መጠለያ ማዕከላት እንዲያርፉ የተደረጉ ዜጎችን ወደ የቀበሌዎቻቸው ሄደው አምራች የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት የእርቀ ሰላምና ሌሎች ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይህን ተግባራዊ ለማድረግም የሰራዊቱ መገለጫ የሆኑ የመከባበርና መደማመጥ መንፈስ በመላበስ የህዝብ ተቀባይነት ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ከቀያቸው ተፈናቅለው በማዕከል የሚገኙ ዜጎችን በአስተማማኝ ሁኔታ ጥበቃ እየተካሄደ በመሆኑም ሰራዊቱ ”ከራስ በላይ ለወገን” የሚለውን መርህ መላበሱን እያስመሰከረ ያለበት ሂደት መሆኑንም አረጋግጠዋል።
መንግሥት ሠራዊቱን ከትግራይ እንዲወጣ የወሰነው ለወታደራዊ ስትራቴጂ ሲባል እንደሆነ ጠቁመውም ሰራዊቱ ህዝባዊነት ስለሚያስገድደው የትግራይ ህዝብ መልሱልን ባለጊዜ ገብቶ አገርና ህዝብን ለመጠበቅ ጽኑ አቋም እንዳለው ገልጸዋል።
በቀጣይም በአውደ ግዳጁ ያሉ የሰራዊት አባላት ጠላት የሚመጣበትን ቀዳዳ ሁሉ በመድፈን ሊሰነዘሩ የሚችሉ ጥቃቶችን ቀድሞ የማክሸፍ ስራ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
የሠራዊቱ አባላት በዚሁ ወቅት እንዳሉትም በየማዕከሉ ያሉ ወገኖችን ሰላምና ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። ኢዜአ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ትግል ለመቀላቀል መወሰናቸውን በአብርሐጅራ የሚገኙ የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ተናገሩ።
Next articleበወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሑመራ ከተማ ዝክረ ሐምሌ 5 እየተከበረ ነው።