
የሀገርን ሰላም ለማስከበር የተንቀሳቀሰው የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል ሽኝት እየተደረገለት ነው።
ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ዛሬ ማምሻውን በሀዋሳ ከተማ ሽኝት መርኃግብር እየተካሄደ ነው።
በመርኃግብሩ ላይ የክልሉ ሰላምና ፈጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቲዎስ፣ የክልሉ ካቢኔዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አቶ ዓለማየሁ እንዳሉት የክልሉ ልዩ ኃይል ወቅቱ ለሚፈልገው ሀገራዊ ተልዕኮ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ግዳጁን እንደሚወጣ ተናግረዋል።
የሀገርን አንድነት ለማፍረስና የሕዝብን የተረጋጋ ሕይወት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
“የልዩ ኃይሉ አባላትም ሀገራዊ ጥሪውን በታላቅ ወኔና ደስታ ተቀብለው ለመዝመት ያላቸው መነሳሳት ከፍተኛ ነው” ብለዋል። ኢዜአ እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ