
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው፡፡
በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ፡፡›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡
ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ሰልፎች በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ፍኖተ ሠላም፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ ደላንታ፣ መርዓዊ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ውጫሌ፣ ወልድያ፣ ላልይበላና ሌሎችም ከተሞች እየተካሄዱ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ፎቶ፡- ኤልያስ ፈጠነ እና ዲያቆን አሰፋ ጌትነት