
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች በፍኖተ ሠላም ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የተናገሩት፡፡
በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ፡፡›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሺባባው -ከፍኖተ ሠላም
ፎቶ፡- አንተነህ ተስፋዬ