
የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና የክልሉ ሥነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተቋማቱ ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም ተቋማቱና ሠራተኞቻቸው የክልሉን የጸጥታ መዋቅር ለማጠናከርና ለህልውና ዘመቻው የሚውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ ለማድረግ ወስነዋል፡፡
የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እንደተቋም 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
የየተቋማቱ ሠራተኞች ከሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ባለፈ በግንባር በመሰለፍ የሕይወት መስዋእትነት ለመከፍል መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።
አዘጋጅ:- ብሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ