
የትህነግ ሽብርተኛ ቡድን የሚፈጽመውን ትንኮሳ ለመከላከል ዝግጅት ማድረጉን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጸጥታ ኃይሉን ስምሪት አጠናክሮ የአሸባሪውን ትህነግ ጠብ አጫሪነት ለመመከት ዝግጁ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ሃምሳ አለቃ አዘዘው አዳነ ገልጸዋል።
የአካባቢው ወጣቶች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችም የዋግን ሰላም ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ መቆማቸውንም ነው የተናገሩት።
የዋግ ሕዝብ የአሸባሪውን ትህነግ የክፋት አካሄዶች ጠንቅቆ ይረዳል ያሉት ሃምሳ አለቃ አዘዘው አሁን ላይ በዋግ ያለው አደረጃጀት የአሸባሪው ትህነግ ጥቃት ከመከላከልም አልፎ ለሀገሩ ዘብ የሚቆም መሆኑን ጠቁመዋል።
“የዋግ ሕዝብ የጸጥታው ዘርፍ ደጀን መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወጣቱም ለአካባቢው ጸጥታ ዓይን እና ጆሮ ሆኖ የሚያገለግል ነው” ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- እሱባለው ይርጋ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ