የሦስትዮሽ ድርድሩ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲቋጭ ኢትዮጵያ በቁርጠኛነት እንደምትሠራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

112
የሦስትዮሽ ድርድሩ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲቋጭ ኢትዮጵያ በቁርጠኛነት እንደምትሠራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የሚያደርጉትን የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል፡፡ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የሚካሄደው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ሀገራቱን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲቋጭ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት ተብሏል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የድርድሩን ሂደት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ከዚህ ቀደም በመርህ ስምምነቱ መሰረት ድርድሩ ሲካሄድ መቆየቱን አስታውሷል።
ድርድሩ ፖለቲካዊ መልክ እንዲይዝ ጥረት በሚያደርጉ አካላት ሲጓተት መቆየቱን የገለጸው የሚኒስቴሩ መግለጫ ኢትዮጵያ ግልጽ አቋሟን አስቀምጣ የድርድር ሂደቱ በፍጥነት እንዲቋጭ ጥረት ማድረጓን አውስቷል። ጉዳዩ ወደማይመለከተው የጸጥታው ምክር ቤት መድረሱ ተገቢ እንዳልነበርም አመላክቷል።
በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር የሚካሄደው የድርድር ሂደት የሁሉንም ወገን ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገባ ውጤት እንደሚያመጣ ተስፋ አለን ብሏል መግለጫው።
“የሦስትዮሽ ድርድሩ ሁሉንም ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲቋጭ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት ትሠራለች” ሲልም መግለጫው አረጋግጧል።
የአፍሪካ ሕብረት በሚያቀርበው ሐሳብ መሰረት ኢትዮጵያ ለድርድሩ ዝግጁ መሆኗን የገለጸው መግለጫው ግብጽ እና ሱዳን ድርድሩ ስኬታማ እንዲሆን በቀናነት እንዲሳተፉ ጥያቄ አቅርቧል።
በታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 56 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
Next article“ለእኛ መኖር ደሙን እየለገሰ ለሚገኘው የጸጥታ ኀይል እንኳን ገንዘብ ከገንዘብ በላይ የሚከፈል ዋጋ ለመስጠት ዝግጁ ነን” የቆቦ ነዋሪዎች