ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 56 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

161
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 56 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 06/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ የተጠቃሚዎቹን ቁጥር ወደ 56 ነጥብ 2 ሚሊየን ማድረሱንም ገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2013 በጀት አመት አፈጻጸምን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ተቋሙ ደንበኞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሲሠራ መቆየቱን ያነሱት ሥራ አስፈጻሚዋ ከ374 ሺህ በላይ ዜጎች በመደበኛ ብሮድባንድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ተቋሙ 56 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰዋል። ይህም የእቅዱ 101 ነጥብ 7 በመቶ ያሳካ መሆኑን አመላክተዋል።
የኀይል አቅርቦት መቆራረጥ ችግሮችም ቢኖሩም በበጀት ዓመቱ ችግሮችን በመፍታት የታሰበዉን ገቢ ማግኘት መቻሉን ነው ሥራ አስፈጻሚዋ የገለጹት።
የማኅበረሰቡን የመክፈል አቅም ታሳቢ በማድረግ የታሪፍ ቅናሽ ከ40 እስከ 86 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ መደረጉን አንስተዋል። ወደ 70 ነጥብ 8 ቢለየን ብር ያክል ክፍያ መፈጸሙን ጠቅሰዉ ከዚህ ዉስጥ 26 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለግብር የተከፈለ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ተግባራት አንዱ የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ ኢንተርኔት አገልግሎት በማስፋፋት በኩል 68 ያክል ከተሞች አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
ተቋሙ ለማኅበራዊ አገልግሎት ከ847 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
በትምህርት፣ በጤና፣ በአረንጓዴ ዐሻራ ልዩ ልዩ ሥራዎች መከናወቸውን አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉዑሽ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኩር ጋዜጣ ሐምሌ 05/2013 ዕትም
Next articleየሦስትዮሽ ድርድሩ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እንዲቋጭ ኢትዮጵያ በቁርጠኛነት እንደምትሠራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡