
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡
በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡
ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ሰልፎች በባሕር ዳር፣ ቢቸና፣ ፍኖተ ሠላም፣ ቡሬ፣ እንጅባራ፣ መርዓዊ፣ ደብረ ብርሃን፣ ማጀቴ፣ ጫጫ፣ ውጫሌ፣ ወልድያ፣ ቆቦ፣ ላልይበላ፣ ደባርቅና ሌሎችም ከተሞች እየተካሄዱ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ሰሎሞን ጥበቡ እና ጋሻዬ ጌታሁን -ከደብረ ማርቆስ