“ለመረጣችኹኝም ላልመረጣችኹኝም ኢትዮጵያውያን ብቁ የሕዝብ ወኪል እና እንደራሴ ለመሆን እጥራለሁ” ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫውን ውጤት ከሰሙ በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት

328

“ለመረጣችኹኝም ላልመረጣችኹኝም ኢትዮጵያውያን ብቁ የሕዝብ ወኪል እና እንደራሴ ለመሆን እጥራለሁ” ሙሐዘ ጥበባት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የምርጫውን ውጤት ከሰሙ በኋላ ያስተላለፉት መልዕክት
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት” ተመረጠ። በርቱዓዊነት መርሕ፥ ፉክክሩ ሲያበቃ
ትብብሩ ይጀምራል።
በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ክልል 28፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በግል ዕጩነት ድምጽ
ማግኘቴን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
በ”ሐ” የምርጫ ምልክት እና “ኢትዮጵያዊነት በርቱዓዊነት” በሚል መርሕ፣ የምርጫ ቅስቀሳ አስተባባሪ ኮሚቴ በማቋቋም ለወራት
ባደረግነው እንቅስቃሴ በልዩ ልዩ ድጋፎች የተራዳችኹኝን፣ በምርጫ ኮሚቴነትና በታዛቢነት ያገለገላችሁትን፣ የገጠማችኹን
ችግሮች ኹሉ ታግሣችኹ ድምፃችኹን የሰጣችኹኝን መራጮቼን በሙሉ ከልብ አመሰግናለኹ።
ይህ ምርጫ ምርጫ እንዲሆን ዋጋ የከፈላችሁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ታሪክ በደማቅ ቀለም ይጽፋችኋል። የተሸነፋችሁም አንዱንና
ዋናውን የኢትዮጵያ ጎደሎ ሞልታችኋል። ኢትዮጵያ በፖለቲካ ፉክክር የተሸናፊ እንጂ የአሸናፊ እጥረት አልነበረባትም። እናንተ
ይሄንን በመሙላት አሸንፋችኋል።
የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ሚዲያዎች፣ ታዛቢዎችና የጸጥታ አካላት ሁሉ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ የከፈላችሁት መሥዋዕትነት
የሀገራችን የክንድ ንቅሳት ሆኖ የሚኖር ነው።
ከሁሉም በላይ ለ12 ሰዓት እንደ ሰዓታት ቋሚ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ ቆሞ የመረጠው ሕዝብ፣ ጠላትን ሐሞቱ ያለቀ፣ ወገንን ልቡ የሞቀ
የሚያደርግ ነበር።
አኹን የፉክክር ወቅት አብቅቷል። ቀጣዩ ጊዜ ለመረጣችኹኝም ላልመረጣችኹኝም ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በርቱዓዊነት
የመተባበር ኢትዮጵያዊ መንፈስ ብቁ የሕዝብ ወኪል እና እንደራሴ ለመኾን የበኩሌን ጥረት የማደርግበት ነውና ጸሎታችኹ እና
ድጋፋችኹ እንዳይለየኝ አደራ እላለኹ። ኢፕድ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሀገር የጋራ ምዕራፍ በመሆኗ የተመረጡ ብቻ ሳይሆን ያልተመረጡም በሀገራቸው ጉዳይ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቀርባለሁ” ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ
Next article“የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍታ በዓለም አደባባይ ጎልቶ የወጣበት ነው” ብልጽግና ፓርቲ