
“ሀገር የጋራ ምዕራፍ በመሆኗ የተመረጡ ብቻ ሳይሆን ያልተመረጡም በሀገራቸው ጉዳይ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቀርባለሁ” ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤትን አስመልክቶ የምርጫ ቦርድ ውጤት መግለጫ መርኃግብር ተካሂዷል፡፡
በመርኃግብሩ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ምርጫ የዲሞክራሲ ግንባታ አንዱ ክፍል እንጂ በራሱ ግብ አይደለም ነው ያሉት።
አሸንፎ መንግሥት የሚመራው ፓርቲ ሁሉንም አሳታፊ በሆነ መንገድ ሀገር ይመራል ብየ አስባለሁ ብለዋል።
የሀገር መረጋጋት ቀዳሚ አጀንዳ በመሆኑ ከምርጫ በኋላ ባሉት ቀናት ቀዳሚ ሥራ ሀገራዊ ሰላምን ማረጋገጥ መሆኑን ጠቁመዋል። ሀገር የጋራ ምዕራፍ በመሆኗ የተመረጡ ብቻ ሳይሆን ያልተመረጡም በሀገራቸው ጉዳይ በጋራ እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር አይገነባም ይልቁንም በሂደት ከስህተቶች መማር ይገባል ያሉት ፕሬዝደንት ሣኅለወርቅ “ሂደቱን አምናችሁ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ ነገም ሌላ ቀን ነው፤ ውድድር ቀጣይ ነው”ብለዋል።
ፕሬዝዳንቷ ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበው ሀገር ከፊቷ ላሉ ፈተናዎች እና መልካም አጋጣሚዎች ሁሉም እንዲዘጋጅ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6