በወልድያ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍ እየተካሄደ ነው፡፡

349

በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና የሃይማኖት አባቶች ሠላማዊ ሠልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠላማዊ ሠልፉ በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ መሆኑ ታውቋል፡፡

በሠልፉ ላይ እየተላለፉ ከሚገኙ መልዕክቶች መካከልም:-
• አጥፊወች ከድርጊታችሁ እንድታተቀቡ እናሳስባለን!
• የቤተ ክርስቲያንን ውለታ መልሱ፤ ባትመልሱ እንኩዋን አትርሱ፡፡
• የክርስቲያኖችን ሞትና ግድያ የዘር ፓለቲካ አታልብሱት፡፡
• ለአገር ሉዓላዊነት ታቦት ይዛ ለምትዋጋ፣ በጸሎት ለምትራዳ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ አይገባትም፡፡
• የመርከቡዋ ተጓዦች ነንና ማዕበል አትቀስቅሱ፡፡
• በአገራችን ባዳ አታድርጉን የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ዘጋቢ፡- ክፍሉ ሞገስ -ከወልድያ

Previous articleየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
Next articleየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች በደብረ ማርቆስ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡