
የደረጃ”ሐ” ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በተያዘለት ጊዜ ከፍለው ማጠናቀቅ እንዳለባቸው የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ አሳሰበ።
አገልግሎቱ ነገን ጨምሮ የሚሰጥ መሆኑን ግብር ከፋዮች አውቀው እንዲከፍሉ ቢሮ አሳስቧል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል 306 ሺህ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን 102 ሺህ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች መቶ በመቶ ከፍለው ማጠናቀቃቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ክብረት መሐመድ ተናግረዋል፡፡ ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለና ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸን ግብር በቅቱ የመክፈል ባሕል እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑን አቶ ክብረት ተናግረዋል፡፡
እስከ አሁን ግብር ያልከፈሉ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የክልሉ መንግሥት ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በተያዘለት ጊዜ ግብር በመክፈል ፈጣን ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል፡፡ ቢሮውም ከባንኮች ጋር ቅንጅት በመፍጠር ለግብር ከፋዮች የተቀላጠፈ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ቢሮው ነገ እሁድን ጨምሮ አገልገሎት ስለሚሰጥ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም የተጣለባቸውን ግዴታ መወጣት እንዳለባቸው ምክትል ቢሮ ኃላፊ አሳስበዋል፡፡
እስከ አሁን ድረስ 22 ወረዳዎች 10 በመቶ ከፍለው ማጠናቀቃቸውን የገለጹት ምክትል ኃላፊው የሥራ ኃላፊዎች፣ የታክስ አምባሳደሮችና የተለያዩ ተቋማት ድጋፍም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ መንግሥትም ከደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የሚገኘው ግብር ቶሎ ተሰብስቦ ለታሰበለት ዓለማ እንዲውል ከፍተኛ ፍላጎት ያለው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ