
“በትልቅ ሀገር ውስጥ ውስን ሎጂስቲክስ ይዞ ምርጫ ማከናውን ከባድ ቢሆንም መፍትሔ ማምጣትና ማረም የሚችሉ ባለሙያዎች በመኖራቸው ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን በስኬት ማከናውን ተችሏል” የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የስድስተኛውሀገራዊ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤትን አስመልክቶ የምርጫ ቦርድ ውጤት መግለጫ መርኃግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ ኀላፊዎች እንደተናገሩት ስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ተጠያቂነት በሰፈነበትና አካታች በሆነ መልኩ ማከናውን መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ ከተሳትፎ አንፃርም የሲቪክ ማኅበራትና የሴቶች ተሳትፎ ጎልቶ የታየበት እንደነበር አስረድተዋል፡፡
በምርጫ ወቅት ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ምላሸ መስጠትና የወጡ ሕጎችን ማስተግበር የተቻለበት ምርጫ እንደነበርም የሥራ ኀላፊዎች ተናግረዋል፡፡
ለዓመታት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲሠሩ የነበሩትን ሠራተኞች በአዲስ በማዋቀር ነጻ፣ ተዓማኒና ሰላማዊ ምርጫ በማካሄድ ሕዝቡ የጣለባቸውን ኀላፊነት መወጣታቸውንም መሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
በ6ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ቦርዱ በአዋጅ የወጡትን ሕጎች ወደ ተግባር የቀየረበትና አደረጃጀቶችን አጠንክሮ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሥራ መሥራት መቻሉንም አስገንዝበዋል፡፡
በጋራ መሥራት ሲቻልም አስቸጋሪ ወቅቶችን በስኬት ማጠናቀቅ እንደሚቻልም ግንዛቤ የተወሰደበት ነው ብለዋል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሜዴቅሳ “በትልቅ ሀገር ውስጥ ውስን ሎጂስቲክስ ይዞ ምርጫ ማከናውን ከባድ ቢሆንም መፍትሔ ማምጣትና ማረም የሚችሉ ባለሙያዎች በመኖራቸው ስድስተኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በስኬት ማካሄድ ተችሏልም” ብለዋል፡፡
በአዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ