የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት በሰው ኀይል እና በቴክኖሎጂ ራሱን በማጠናከር የማኅበረሰብ አገልግልት እንደሚሰጥ ገለጸ፡፡

131
የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት በሰው ኀይል እና በቴክኖሎጂ ራሱን በማጠናከር የማኅበረሰብ አገልግልት እንደሚሰጥ ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር: ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት መግለጫ መርኃግብር እየተካሄደ ነው፡፡ በመግለጫው ላይ በምርጫ ሂደቱ ተሳትፎ የነበራቸው የሲቪክ ማኅበራት፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡
በስድስተኛው ሀገርአቀፍ ምርጫ 46 የሚጠጉ የሀገር ውስጥ ሲቪክ ማኅበራት ምርጫውን በመታዘብ ተሳታፊ ነበሩ፡፡ 169 ሲቪክ ማኅበራት ደግሞ የመራጮች ትምህርት መስጠታቸው ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበራት ሕብረት ለምርጫ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ተሳትፎ አድርጓል ያሉት የማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ታምራት ከበደ የተሳተፉባቸው ዘርፎች በመራጮች ትምህርት፣ በምርጫ ትዝብት እና በሚዲያ ሞኒተሪንግ ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በቅድመ ምርጫ ሂደት 117 ሰልጣኝ፣ የቅድመ ምርጫ ሂደት ታዛቢዎች በ1 ሺህ 300 የምርጫ ጣቢያዎች በመሰማራት ጥንካሬዎችን፣ ድክመቶችን እና መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችን በመለየት ሪፖርት መደረጉን አቶ ታምራት ገልጸዋል፡፡
በምርጫ ቀንም ከ2 ሺህ 400 በላይ ሰልጣኝ ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ታዛቢዎች በ2 ሺህ 500 ጣቢያዎች በመንቀሳቀስ ሂደቱን ተከታትለዋል ነው የተባለው፡፡
የምርጫው ቀን ሂደትም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት በዕለቱ ለማኅበሩ እንደደረሰው እና የተጠቃለለ ሪፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ መድረሱን አብራርተዋል፡፡
110 የረጅም ጊዜ ታዛቢዎች የድህረ ምርጫ ሂደቱን እየታዘቡ እንደሆነ የጠቆሙት የቦርድ ሰብሳቢው ማኅበሩ ራሱን በሰው ኀይል እና በቴክኖሎጂ እያጠናከረ ከዚህ የበለጠ የማኅበረሰብ አገልግልት ይሰጣልም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሲካሄድ እንደሀገር ችግሮች ቢኖሩም ቦርዱ የዜጎችን ድምጽ ወደ ሥልጣን ለመቀየር መደረግ ያለበትን ሂደት አከናውኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል” የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ
Next article“የዛሬው የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ውጤት መግለጫ ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ ነው” አምባሳደር ስቴፋን አዎር