
“ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሲካሄድ እንደሀገር ችግሮች ቢኖሩም ቦርዱ የዜጎችን ድምጽ ወደ ሥልጣን ለመቀየር መደረግ ያለበትን ሂደት አከናውኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል” የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የስድሰተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የመጀመሪያ ደረጃ የመራጮች ድምጽ አጠቃላይ ውጤት ይፋ ማድረጊያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በአዲስ አበባ ከፍተኛ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች፣ የማኅበራዊ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ “ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ሲካሄድ እንደሀገር ችግሮች ቢኖሩም ቦርዱ የዜጎችን ድምጽ ወደ ሥልጣን ለመቀየር መደረግ ያለበትን ሂደት አከናውኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል” ነው ያሉት፡፡
ምርጫው ሲካሄድ ብዙ ሀገራዊ ውጣ ውረዶች፣ የዜጎች የጸጥታ ስጋት፣ ጸጥታው ባልተረጋጋበትና ሌሎችም ችግሮች በበዙበት የዜግነት መብት ለመጠቀም፣ ሀገር መሆናችንን ለማሳየትና ግዴታችንም ለመወጣት ቦርዱ ባስቀመጠው መርኃግብር ምርጫው መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ሂደትም ተሳትፎ ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል ዋና ሰብሳቢዋ።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ